Man Ende Kal

歌手: Eyob Mekonen • 专辑:Ende Kal • 发布时间:2010-09-01
作词 : RR
 作曲 : RR

ውል አይጻፍ ከእኛስ ደጃፍ
ቅንጣት ላይተርፍ ፍቅር ቢቀር ቢከንፍ
ልብ ይበቃል መቆም ለቃል
ቤት ይሞቃል በቃል በቃል በቃል

ወረቀት ምን ሊያድን
ፍቅር ቢሆን በድን
ንገሪኝ አምናለሁ
ቃልሽን አከብራለሁ

ውል አይጻፍ ከእኛስ ደጃፍ
ቅንጣት ላይተርፍ ፍቅር ቢቀር ቢከንፍ
ልብ ይበቃል መቆም ለቃል
ቤት ይሞቃል በቃል በቃል በቃል

ወረቀት ምን ሊያድን
ፍቅር ቢሆን በድን
ንገሪኝ አምናለሁ
ቃልሽን አከብራለሁ

ልቤ ማን ገፍቶት አንቺን አለ
ያኔ ሳያምንበት መች ማለ
በህልሜም በውኔም ካንቺው ጋራ ነኝ
ለይኔ ሌላ አልመች አማረኝ

ፍቅሬን በወረቀት መች ፃፍሽው
እግሬን በፍቅርሽ ነው ያሰርሽው
ነፍሴ አካሌ ነሽ የጎኔ
ዶሴ ከኔ በላይ ለምኔ

ያመንኩሽ ያኔ ነው ተረጋግቶ
ውል አለኝ ሲል ልቤ ቃልሽን ሰምቶ
እርስቴም ፍቅርሽ ነው ውስቴ ገብቶ
በቁሜ አውርሶሻል ልቤን ገዝቶ

ውል አይጻፍ ከእኛስ ደጃፍ
ቅንጣት ላይተርፍ ፍቅር ቢቀር ቢከንፍ
ልብ ይበቃል መቆም ለቃል
ቤት ይሞቃል በቃል በቃል በቃል

ወረቀት ምን ሊያድን
ፍቅር ቢሆን በድን
ንገሪኝ አምናለሁ
ቃልሽን አከብራለሁ

የእውነት የፍቅር ፅዋ በለስ
አምኖ ሳያምንበት የማይደርስ
መጣው ብዬ ቆሜ ከደጅሽ
ላድር ነው አንቺ ውስጥ በልብሽ

ስጋት የሌለው የተቃና
ለኛ ፍቅራችን ዋስ አለና
የኔ የምለውም ያንቺው ነው
ሌላው ምስክር የማያየው

ያመንኩሽ ያኔ ነው ተረጋግቶ
ውል አለኝ ሲል ልቤ ቃልሽን ሰምቶ
እርስቴም ፍቅርሽ ነው ውስቴ ገብቶ
በቁሜ አውርሶሻል ልቤን ገዝቶ

ያመንኩሽ ያኔ ነው ተረጋግቶ
ውል አለኝ ሲል ልቤ ቃልሽን ሰምቶ
እርስቴም ፍቅርሽ ነው ውስቴ ገብቶ
በቁሜ አውርሶሻል ልቤን ገዝቶ

ያመንኩሽ ያኔ ነው ተረጋግቶ
ውል አለኝ ሲል ልቤ ቃልሽን ሰምቶ
እርስቴም ፍቅርሽ ነው ውስቴ ገብቶ
በቁሜ አውርሶሻል ልቤን ገዝቶ
📥 下载LRC歌词 📄 下载TXT歌词

支持卡拉OK同步显示,可用记事本编辑