Debzizeshe

歌手: Eyob Mekonen • 专辑:Ende Kal • 发布时间:2008-06-12
作词 : RR
 作曲 : Eyob Mekonen


መልክን የሻረዉ
አንቺ ጋር ምን ተሻለው
ከሩቅ ሳትስቢ
አየሁ ልቤ ስትገቢ

ካንቺ በላይ ቆንጆ ሞልቶ
ያዉቃል ልቤም ቀርቦም አይቶ
ግን በምን በለጥሻቸው
ቆንጆዎቹን አስናቅሻቸው

ካንቺ በላይ እዉቀታቸው
ስቄም ነበር በቀልዳቸው
ዝምታሽ በለጣቸው
ደብዝዘሽ አጋለጥሻቸው

መልክን የሻረዉ
አንቺ ጋር ምን ተሻለው
ከሩቅ ሳትስቢ
አየሁ ልቤ ስትገቢ

ካንቺ በላይ ቆንጆ ሞልቶ
ያዉቃል ልቤም ቀርቦም አይቶ
ግን በምን በለጥሻቸው
ቆንጆዎቹን አስናቅሻቸው

ካንቺ በላይ እዉቀታቸው
ስቄም ነበር በቀልዳቸው
ዝምታሽ በለጣቸው
ደብዝዘሽ አጋለጥሻቸው

ለኔው ጥቅም በኔው ሰው ተመክሬ
አላውቅም አብልጬ ከልብ አምርሬ
አሁን ለምን ገባኝ ባንቺ ስመከር
ያሉኝን ብለሺኝ የምፍጨረጨር

ከኔ ነው ወይ ካንቺ ነው
ልቤን ለጅሽ የሰጠነዉ

ማኩረፍ የኔ ነበር አልሸፋፈንኩም
ካንቺ ጀምሬ ግን አልተቀየምኩም
ምንድነው ብርቅ ሆኖ የሚያስወድደኝ
ሁሉሽን እንዳደንቅ የሚያስገድደኝ

የት ብለው የት ቢሄዱ
መስፈርት የለም ከወደዱ

መልክን የሻረዉ
አንቺ ጋር ምን ተሻለው
ከሩቅ ሳትስቢ
አየሁ ልቤ ስትገቢ

ካንቺ በላይ ቆንጆ ሞልቶ
ያዉቃል ልቤም ቀርቦም አይቶ
ግን በምን በለጥሻቸው
ቆንጆዎቹን አስናቅሻቸው

ካንቺ በላይ አውቀታቸው
ስቄም ነበር በቀልዳቸው
ዝምታሽ በለጣቸው
ደብዝዘሽ አጋለጥሻቸው

ተቀይሯል አይኔ ወዷል መልክሽን
ሲመዝኑሽ ያደንቃል ሲቀርቡሽ አንቺን
ቆንጆም ዉብም ለኔ ያንቺ አይነት ብቻ
ባይም ልቤ አያምንም እንዳለሽ አቻ

የት ብለው የት ቢሄዱ
መስፈርት የለም ከወደዱ

ተቀይሯል አይኔ ወዷል መልክሽን
ሲመዝኑሽ ያደንቃል ሲቀርቡሽ አንቺን
ቆንጆም ዉብም ለኔ ያንቺ አይነት ብቻ
ባይም ልቤ አያምንም እንዳለሽ አቻ

ግን በምን በለጥሻቸው
ቆንጆዎቹን አስናቅሻቸው
ዝምታሽ በለጣቸው
ደብዝዘሽ አጋለጥሻቸው

ግን በምን በለጥሻቸው
ቆንጆዎቹን አስናቅሻቸው
ዝምታሽ በለጣቸው
ደብዝዘሽ አጋለጥሻቸው

ግን በምን በለጥሻቸው
ቆንጆዎቹን አስናቅሻቸው
ዝምታሽ በለጣቸው
ደብዝዘሽ አጋለጥሻቸው
📥 下载LRC歌词 📄 下载TXT歌词

支持卡拉OK同步显示,可用记事本编辑