Nekichalew

歌手: Eyob Mekonen • 专辑:Ende Kal • 发布时间:2008-06-12
作词 : RR
 作曲 : Eyob Mekonen


ነቅቻለሁ ተርፊያለሁ
እራሴን ላድን ቆርጫለሁ
ልኩ ላይ ብርሀኑ ላይ
አይኔ ላይፈዝ ጨለማው ላይ

ልፈልገው ከዋለበት
ፍፁም ፍቅር ከሞላበት
እራሱ ላይ ጎዳናው ላይ
ፍቅርን ላገኝ ፊት ለፊት ላይ

መቼ ተሞኘ ብልህ ነው ፍቅር
ክብሩን አይጥልም ከውሸት መንደር
ከቅብዝብዝ ጋር መች ይረጋጋል
አይታለልም ሸንጋዩን ያውቃል

መንገዴ ለየ አይኔ ብርሀን አየ
መንገዴ ለየ አይኔ ብርሀን አየ
በቃ በቃ ድሮ
የጨለማው ኑሮ
በቃ በቃ ዱሮ
የጨለማው ኑሮ
በቃ በቃ ሆሆሆ
በቃ በቃ ይዬዬ

ነቅቻለሁ ተርፊያለሁ
እራሴን ላድን ቆርጫለሁ
ልኩ ላይ ብርሀኑ ላይ
አይኔ ላይፈዝ ጨለማው ላይ

ልፈልገው ከዋለበት
ፍፁም ፍቅር ከሞላበት
እራሱ ላይ ጎዳናው ላይ
ፍቅርን ላገኝ ፊት ለፊት ላይ

የተራበ ልብ ፍቅርን ይጏጏል
ከእውነት ቤት ሄዶ እውነት ያንኳኳል
ደጁን ለጠና እዛው ቆይቶ
የራሱ ያቅፋል በሩ ተከፍቶ

መንገዴ ለየ አይኔ ብርሀን አየ
መንገዴ ለየ አይኔ ብርሀን አየ
በቃ በቃ ድሮ
የጨለማው ኑሮ
በቃ በቃ ዱሮ
የጨለማው ኑሮ

በቃ በቃ ሆሆሆ
በቃ በቃ ይዬዬ
በቃ በቃ ሆሆሆ
በቃ በቃ ይዬዬ
📥 下载LRC歌词 📄 下载TXT歌词

支持卡拉OK同步显示,可用记事本编辑